All updates

DW: በኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት የኤርትራ የቀድሞ አምባሳደር አስተያየት

10/07/2018

በኢትዮ ኤርትራ አዲስ ግንኙነት በተመለከተ የቀድሞ የኤርትራ አምባሳደርን እና የቀድሞ የአስመራ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ምክር ቤት አባልን አስተያየት ጠይቀናል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ስምምነት በመቀበል ከኤርትራ ጋር ሰላም ለመፍጠር ባስታወቀዉ መሠረት ከኤርትራጋ ያለዉን የወዳጅነት ግንኙነት ቀስ በቀስ እያጠናከረ ነዉ። በሁለቱ ሃገራት የወዳጅነት መንግሥታት ተጠሪዎች መካከል ብቻ ሳይሆን በሁለቱም ሃገራት ሕዝቦች መካከል በጉልህ እየታየ ነዉ። ብረስልስ የሚገኘዉ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአስመራን ጉብኝት አስመልክቶ በቤልጂየም የቀድሞ የኤርትራ አምባሳደርን እና የቀድሞ የአስመራ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ምክር ቤት አባልን አስተያየት ጠይቆ ዘገባ ልኮልናል።


AUDIO: 

DW Amharic: በኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት የኤርትራ የቀድሞ አምባሳደር አስተያየት