DW: «የሁለቱ መንግሥታት መቀራረብ ፈጣን ነዉ»

26/06/2018

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ 20 ዓመት ያስቆጠረዉን የድንበር ላይ ጦርነት፤ ግጭትና ዉዝግብ ለማስወገድ የጀመሩትን አንድ የቀድሞ የኤርትራ ዲፕሎማት «ጠቃሚ» እና ተገቢ በማለት አወደሱት።

በቤልጅግ እና በአዉሮጳ ሕብረት የቀድሞዉ የኤርትራ አምባሳደር ዓንደብርሃን ወልደ ጊዮርጊስ እንደሚሉት የሁለቱ መንግሥታት መቀራረብ ከሚታሰበዉ በላይ ፈጣን ለዉጥ የታየበት ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ የዴሞክራሲያዊ ለዉጥ ኤርትራ ዉስጥ ይደረጋል ተብሎ ለሚታሰበዉ የዴሞክራሲዊ የለዉጥ ሒደት አወንታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ዲፕሎማቱ ተስፋ አላቸዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ አምባሳደር ዓንደብርሃንን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

AUDIO: 

DW Amharic: «የሁለቱ መንግሥታት መቀራረብ ፈጣን ነዉ»